“የኢንዱስትሪ ምርቶችን ይበልጥ ለማሳደግና የሥራ እድልን ለመፍጠር፣ ለማዘመንና ተወዳዳሪ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ነው” አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ

63

አዲስ አበባ: ጳጉሜን 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “ኢትዮጵያ የራሷ ብራንድ ይገባታል” በሚል የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕን አምራችነት ለማሳደግ የባለ ድርሻ አካላት የምክክር መድረክና ኤግዚቢቪሽን በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ

የኢንዱስትሪ ምርቶችን ይበልጥ ለማሳደግና የሥራ እድልን ለመፍጠር፣ ለማዘመንና ተወዳዳሪ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት በርካታ ኢንዱስትሪዎች ከኪሳራ በመውጣት ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን ምርት እንዳመረቱ አምባሳደር ሱሌማን ለተወያዮቹ አብራርተዋል።

የቀድሞው ብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ግዙፍ ሀገራዊ ሀብት አሰባስቦ ለበጎ ሀገራዊ ዓላማ የተቋቋመ ቢሆንም በብልሹ አሠራር ምክንያት ሀገራችንን በመቶ ቢሊዮኖች ብር ያሳጣ ተቋም ሆኖ አልፏል፤ በዚህ ምክንያት በሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ነው ያሉት።

ከሀገራዊ ለውጥ በኋላ መንግሥት ይሄንን ተቋም ሪፎርም በማድረግ ከዚህ በፊት የደረሠውን ጥፋት መካስ በሚችልበት መንገድ ተደራጅቷል ብለዋል።

በመሆኑም ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ተልዕኮውንና ዓላማውን በአዲስ መልክ በመከለስ መስከረም 6/2013 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 475/13 እንዲቋቋም በማድረግ ከፍተኛ ክፍተት ያለበት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት የሚችሉ የማኑፋክቸሪንግ ውጤቶች ላይ በትኩረት እየሠራ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል።

ዘጋቢ:–ሳሙኤል ኪሮስ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከሸማችነት ወደ አምራችነት!!
Next articleየልማት ቀንዲል የበጎ ሥራ ተምሳሌት ክቡር ዶክተር ዓለማየሁ ስመኝ የምሥጋና መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ተካሄደ ።