“የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተቋማዊ አደረጃጀት ተፈጥሮለታል” የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

45

ባሕር ዳር: ጳጉሜን 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ዘርፉን በዘላቂነት እንዲደግፍ ተቋማዊ መዋቅር እንዲዘረጋለት መደረጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የአምራቹ ዘርፍ የአገሪቱ የዕድገት ምሰሶ ተብለው ከሚጠቀሱ መስኮች መካከል አንዱ ነው።

በ10 ዓመቱ መሪ ዕቅድ መጀመሪያ ላይ 30 በመቶ ድርሻ የነበረውን የአምራች ዘርፍ የገበያ ድርሻ በዚህ ዓመት 34 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ 37 በመቶ ማድረስ መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

መንግስት ዘርፉ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን ድርሻ ያሳድጋሉ ያላቸውን የማሻሻያ እርምጃዎች እየወሰደ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አንዱ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ነው።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሚያዚያ 29/2014 መጀመሩ ይታወቃል።

ንቅናቄው የአምራች ኢንዱስትሪውን ዕድገትና ተወዳዳሪነት ማሳደግ እንዲሁም አምራቾችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት ያለመ ነው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በንቅናቄው የአገር ውስጥ አምራቾች ምርታማነት ላይ ለውጦች መታየታቸውንና ባለሀብቶች በዘርፉ የመሰማራት ፍላጎታቸው መጨመሩን ለኢዜአ ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአፋር ክልል ርእሰ-መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ጳጉሜን 4 የምርታማነት ቀንን በዱብቲ ወረዳ ለምግብነት የሚውሉ የችግኝ ተከላ አካሄዱ ፡፡
Next articleየምርት ብክነት እንዳያጋጥም የድሕረ ምርት አያያዝ ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት እንደሚገባ ግብርና ቢሮ አሳሰበ፡፡