የአፋር ክልል ርእሰ-መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ጳጉሜን 4 የምርታማነት ቀንን በዱብቲ ወረዳ ለምግብነት የሚውሉ የችግኝ ተከላ አካሄዱ ፡፡

35

ባሕር ዳር: ጳጉሜን 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሀጂ አወል አርባ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ጳጉሜን 4 የምርታማነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በዱብቲ ወረዳ የምግብነት ይዘት ያላቸው ችግኝ ተከላ መርሐ – ግብር አከናውነዋል ፡፡

ርእሰ መሥተዳድር ሃጂ አወል አርባ ለአፋር ቴሌቪዥን እንደገለጹት አዲሱን የ2016 አመት በተሻለ መነሳሳት ለመቀበል የጳጉሜ ቀናትን በተለያዩ ስያሜዎች ተሰይመው ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በመሆን በተለያዩ በጎ ተግባራት እያሳለፍን እንገኛልን።

በዚህም መሰረት ዛሬየ ምርታማነት ቀንን ምክንያት በማድረግ እለቱን በዱብቲ ወረዳ የተለያዩ ምግብነት ይዘት ያላቸው ቋሚ ተክሎች ችግኝ ተከላ በማካሄድ ጀምረናል ፡፡

በመረሀ ግብሩም ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ ችግኝ ተከላ የተካሄደ ሲሆን ይህ በየደረጃ ሁሉም ከግለሰብ እስከ ሀገር ድረስ በየደረጃው በተሰማራበት ሙያ ምርታማነትን ለማሳደግ የበኩን መወጣት ይጠበቅበታል።
በዚህም አግባብ መርሃ ግብሩ አንደሀገርና ማኅበረሰቡን ከኋላ ቀርነትና ድህነት በተፋጠነ ጊዜ በመውጣት ሀገራዊ እድገትና ብልጽግናን እውን ለማድረግ ያስችላል ብለዋል ፡፡

በእለቱ የችግኝ ተከላ በ20ሄክታር ላይ ሲያከናውኑ ያገኘናቸው ልማታዊ ባለሃብት አቶአህመድ አሊ በበኩላቸው የቋሚ ተክል ልማቱ ላይ በዚህ ዓመት ጀምረው ወደስራ የገቡ መሆኑን ገልጸዉ ስራው ውጤታማ የሚያደርግ በመሆኑ ሌሎች ባለሃብቶችም በዘርፉ ቢሰማኑ እራሳቸውን ጠቅመው ኅብረተሰቡ እየገጠመው የሚገኘውን የኑሮውድነት ለማቃለል ጉልህሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።

በመቀጠልም የአፋር ክልል ርእሰ-መሥተዳድር ሀጂ አወል አርባ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የዱብቲ ወረዳ ችግኝ ተከላ መርሃግብርን አጠናቀው ወደ በአይሳኢታ እና አካባቢው ተጉዘው ጳጉሜ 4 የምርታማነት ቀንን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ክንውኖችን በማድረግ ላይ ናቸው ፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ህሊና አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንደስትሪ ኢትዮጵያ ከሸማችነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገሯ ምሳሌ የሚኾን ነው” የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ከሚል
Next article“የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተቋማዊ አደረጃጀት ተፈጥሮለታል” የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር