“ህሊና አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንደስትሪ ኢትዮጵያ ከሸማችነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገሯ ምሳሌ የሚኾን ነው” የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ከሚል

96

አዲስ አበባ: ጳጉሜ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “ከሸማችነት ወደ አምራችነት” በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ ጳጉሜ 4/2015 ዓ.ም የሚከበረው የአምራችነት ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በህሊና አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።
በዝግጅቱ ላይ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሙፈሪያት ከሚል ህሊና ገንቢ ምግቦች ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ፋብሪካ እና የብሌስ አግሮ ፉድ ላብራቶሪ ዛሬ ለሚከበረው የአምራቾች ቀን ኢትዮጵያ ከሸማችነት ወደ አምራችነት መሸጋገሯ ምሳሌ የሚኾንና በተግባር የሚያሳይ ነው ብለዋል። ለዚህም ምሥጋና አቅርበዋል::

የህሊና አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ሥራ አሥኪያጅ ህሊና በለጠ ኩባንያው ይህንን በዓል እንዲያዘጋጅ መመረጡ ያለውን የዳበረ ልምድ ለተሳታፊዎች ለማካፈል ልዩ ዕድል እንደፈጠረለት አስረድተዋል።

ኩባንያው የተቋቋመበት ዋና ዓላማ በሕፃናት ላይ የሚታየውን የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረትን ለመፍታትና በሀገር ውስጥ ለማምረት እንደኾነ አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ:- ቤቴል መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአምራችነት ቀንን አስመልክቶ ሚኒስትሮች ፋብሪካ ጎበኙ።
Next articleየአፋር ክልል ርእሰ-መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ጳጉሜን 4 የምርታማነት ቀንን በዱብቲ ወረዳ ለምግብነት የሚውሉ የችግኝ ተከላ አካሄዱ ፡፡