
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “ከሸማችነት ወደ አምራችነት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ የሚገኘውን የአምራችነት ቀንን አስመልክቶ ሚኒስትሮች በፋብሪካ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል።
የኢንዱስትሪ፣ የሥራ እና ክህሎት፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር፣ የማዕድን እና ገቢዎች ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴዔታዎች እና የተቋማቱ አመራሮች የፋብሪካ ጉብኝት አድርገዋል።
በጉብኝታቸውም፣ አምራች ኢንዱስትሪዎቹ ያሉባቸውን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት በሚያስችሉ የመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያ መመካከራቸውን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች በተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ለመፍታት የሚያስችል ጉብኝት እንደነበር የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!