
👉 በአማራ ክልል የተፈጠረውን የሰላም እጦት ለመፍታት በተሠሩ ሥራዎች አንፃራዊ ሰላም እየተፈጠረ ነው።
👉የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ በርካታ ታጣቂዎች ተፈጥረዋል፤ ታጣቂዎቹ ወደ መደበኛ ሕይወት እንዲመለሱ ፣ በመንግሥት የፀጥታ መዋቅር እንዲካተቱ ብዙ ሥራ ተሠርቷል።
👉 አስቸኳይ ጊዜ በመታወጁና በቅንጅት በመሠራቱ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ተፈጥሯል።
👉 ሕዝቡ ሰላም በመፈለጉና ጦርነትን በመሰልቸቱ ክልሉ በፍጥነት ወደ ሰላም ተመልሷል።
👉 የአማራ ሕዝብ ሰላም እንዲቀጥል ፤ ግጭት እንዲቆም የተሠራው ሥራ ታሪክ የማይረሳው ፤ የአማራን ሕዝብ ሥነ ልቦና የሚመጥን ነው።
👉ሕዝቡ የጀመረውን የሰላም ሥራ አጠናክሮ ከሄደ በአጭር ጊዜ ወደ ፍጹም ሰላም መመለስ ይቻላልም ነው ያሉት።
👉 ፖለቲከኞችም ኾነ ሌሎች አካላት ለዜጎች ሰላም መሥራት እና ከአባባሽ ነገሮች መራቅ አለባቸው።
👉 መጀመሪያችንም መጨረሻችንም የሕዝብ ሰላም መኾን አለበት። አሁን ላይ ክልሉ ከችግር እየወጣ ነው።
👉 የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ በዲሞክራሲ አግባብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር መታገል አለበት።
👉 ክልሉን የሚመጥን የሕዝቡን ሥነ ልቦና እያየ ጥያቄዎችን መመለስ የሚያስችል መሪ ማደራጀት ስላስፈለገ ከክልሉ ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ መሪዎችን የማደራጀት ሥራ እየተሠራ ነው።
👉ከሕዝብ ጋር መግባባትና በሁሉም ነገር ሕዝብን ባለቤት ማድረግ ወሳኝ በመኾኑ ከሕዝብ ጋር መወያየት ፣ በግልፅ መነጋገርና መግባባት ያስፈልጋል።
👉 የተፈጠረው አለመረጋጋት የአማራን ሕዝብ አይመጥንም፤ የአማራ ሕዝብ ከግጭት ወጥቶ የተጠማውን ልማት ማግኘት አለበት።
👉 ወደ ልማት ሳይገባ ኢኮኖሚን ማሳደግ ሳይቻል ጥያቄዎችን መመለስ አይቻልም። ለአማራ ሕዝብ የተጠማውን ልማት መስጠት ግድ ይላል።
👉 ሕዝቡን እያማረሩ ያሉ የመልካም አሥተዳደር ችግሮች መፈታት አለባቸው። መፍታት ሲገባን ያልፈታናቸው ችግሮች እየበዙ በመምጣታቸው ሕዝቡ ተቀይሞናል። ከላይ እስከታች ያለው መዋቅር ከጥላቻ ነፃ ኾኖ ለአካባቢው ሰላምና ልማት መጨነቅ ፣ የሕዝብ እንባ ማበስ አለበት።
👉መፍታት የሚገባንን ሳንፈታ ከሄድን ሕዝብን እያስቀየምን እንሄዳለን፣ ሕዝብ ሲቀየም ደግሞ ለአመራር እንቸገራለን። አዳዲስ መሪዎችም ኾኑ በሕዝብ ታምኖባቸው የሚቀጥሉ መሪዎች ለሕዝብ ጥቅም መሥራት አለባቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!