‹‹በጊዜያዊነት የሚሠሩ በጎ ተግባራትን ዘላቂ ማድረግ ይገባል›› ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ

56

ባሕር ዳር: ጳጉሜን 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የበጎነት ቀን ሲከበር ክፋትን፣ ስግብግብነትን፣ ለብቻ መኖርን በማስወገድ ከማኅበረሰቡ በተለይም ደግሞ ከግፉዓን ጋር በተግባር ለመገናኘት ታስቦ መኾኑን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የመጣውን መተሳሰብ እና በጎ ምግባር እንዲያድግ ያደርጋል ብለዋል፡:

በጎነት በሃይማኖታዊ እና ግብረገባዊ እሴትነቱ ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው መልካም ተግባር በመኾኑ ለአቅመ ደካሞች እና ለሀገር ተረካቢ ታዳጊዎች ማገዝ ይገባል ብለዋል።

‹‹መተሳሰብ ሲተርፍ በምንሰጠው ቁስ ብቻ የሚገለጽ ሳይኾን በሃሳብም በማገዝ በማኅበረሰቡ የሚታዩ ችግሮችን መቀነስ ይገባል›› ብለዋል ርእሰ መሥተዳደሩ፡፡

የመረዳዳትና የመተጋገዝ ባሕሉ ዘላቂነት እንዲኖረው ተቋማዊ እና ማኅበራዊ መሠረት እንዲይዝ ማድርግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በጎነት ላይ በተለይም ደግሞ ማኅበረሰቡ ላይ የሚሠሩ ተቋማት፣ ረጅ ድርጅቶች እና በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ አደረጃጀቶች ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ አስገንዝበዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የክልሉ መንግሥት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በጎነት ለራስ ዞሮ ይከፍላል”
Next article“ሰማያዊ ካልኾነ በስተቀር ምድራዊ ሰው ይሄን ሥራ እንደማያስተወኝ አምናለሁ፡፡” ብርሃን መልካሙ