ርዕሰ መሥተዳድሩ እና ልዑካቸው ሞጣ ከተማ ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን መስጊዶች እየጎበኙ ነው።

664

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ በሞጣ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የተቃጠሉ መስጊዶችን እና የንግድ ተቋማትን እየጎበኙ ነው።

በሞጣ ከተማ አስተዳደር ታህሳስ 10/2012 ዓ.ም በመስጊዶች እና በግለሰቦች የንግድ ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳት እየጎበኙ ከሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች ውስጥ የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እና የርዕስ መስተዳድሩ የህዝብ አደረጃጀት አማካሪ አቶ አብርሃም አለኸኝ ይገኙበታል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ጉዳት ከደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እና የከተማው ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፎቶ፦ ከሞጣ ከተማ አስተዳድር ኮሙኒኬሽን ገጽ

Previous article“በብሄሩ ወይም በሃይማኖቱ ውክልና ተሰጥቶት የመጣ ተማሪ የለም።” የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
Next article“እንግዶች ልክ ወደ ቤታቸው እንደመጡ እንዲሰማቸው የሚያደርግ ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቀናል፡፡” የጎንደር ከተማ አሥተዳድር