
ባሕር ዳር: ጳጉሜ 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ትጫወታለች።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ከግብጽ ጋር ያደርጋል።
የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ በካይሮ ‘ሰኔ 30 ስታዲዬም’ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ይከናወናል።
በጊዜያዊ ዋና አሠልጣኝ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለጨዋታው ከነሐሴ 23 እስከ 28/2015 በአዲስ አበባ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!