
አዲስ አበባ: ጳጉሜ 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የመሥዋዕትነት ቀን በመሥዋዕትነት የምትፀና ሀገር ኢትዮጵያ በሚል መሪ መልእክት የመከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከፍተኛ መሪዎች የፌደራል የፀጥታ ኅይሎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ዋና መሥሪያ ቤት በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።
የመከላከያ ሚንስትር ድኤታ ማርታ ሉዊጂ ኢትዮጵያ የሀገር ህልውናን የሚፈታተን የሕዝብን ሰላም የሚነሳ ችግር ሲያጋጥም በመሥዋዕትነት ሀገርን እያፀኑ የሚሄዱ ጀግና ልጆች አሏት ብለዋል።
ዘጋቢ:- ቤተልሄም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!