
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ ባለፈው ዓመት በጀመርነው ‘የሌማት ትሩፋት’ ውጥን፣ዘመናዊ ዘዴዎችን ስራ ላይ በማዋል የማር ምርታማነትን በዓመት ወደ 98 ሺህ ቶን ማሳደግ ችለናል።
ኢትዮጵያ የተለያዩ ዕፅዋት ያሉባት ሀገር እንደመሆኗ እና የተለያዩ ሥነ-ምህዳራዊ እና የአየር ንብረት ሁኔታዎች ለማር ምርት ምቹ ስለሚያደርጓት፣ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት የቀጣይ ዓመት ዕቅዳችን አመታዊ ምርትን በእጥፍ ማሳደግ ነው። አሁንም ለተሻለ ምርት የምናደርገውን ጥረት አብረን እናጠናክር።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!