ጳጉሜን 2 የመስዋዕትነት ቀን በተለያዩ መርሐ ግብሮች ዛሬ ይከበራል።

39

ባሕር ዳር: ጳጉሜን 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጳጉሜን 2 የመስዋዕትነት ቀን በመላው ኢትዮጵያ “በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ዛሬ ይከበራል፡፡

ጠዋት 5 ሰዓት ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባለበት ቆሞ ቀኝ እጅን ወደ ላይ በማንሳት”እኔ የኢትዮጵያ የፀጥታ፣ የመረጃ እና የደኅንነት ተቋማት ለከፈሉት እና እየከፈሉት ላለው መስዋዕትነት ክብር እሰጣለሁ!” የሚል መልዕክት እንደሚያስተላልፍ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት ዘርፍ ለሀገሩ የሚጠበቅበትን መስዋዕትነት ለመክፈል በብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃል እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በ41 ዓመታት የሕክምና አገልግሎት ሦስት ቀናት ብቻ እረፍት”
Next articleበጀግኖች ሰማዕታት ደም ደምቃ በአፅማቸው ፍላፃ የተማገረች ሀገር ኢትዮጵያ!!