
ባሕር ዳር: ጷጉሜን 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በውስጡ ያሉ የተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶች ተወካዮች ወደ አማራ ክልል ገብተዋል።
ወደ አማራ ክልል ከገቡት ተወካዮች መካከል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ራሚዝ አልአክባሮቭ (ዶ.ር)፣ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ተወካይ ሚካኤል ሳድ፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የሥነ ሕዝብ ድርጅት (UNFPA) ምክትል ተወካይ ያይዎ ኦሉዮሚ፣ የኬር የሀገር ውስጥ ዳይሬክተር ካትሊን ጎጊን እና የተመድ የጸጥታ ዋና አማካሪ ፕሪንስ ብሩስ ይገኙበታል።
ተወካዮች በባሕርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ተወካዮች በሚኖራቸው ቆይታ ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጋር በባሕርዳር ከተማ የፓናል ውይይት ያካሂዳሉ ተብሏል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!