“ከአፍሪካ ዋንጫው ብንሰናበትም ግብፅን ለማሸነፍ በሙሉ አቅም እንጫወታለን” አሠልጣኝ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም

35

ባሕር ዳር: ነሐሴ 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2023 በኮትዲቫር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን የፊታችን አርብ ጳጉሜን 3 ከግብፅ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል።

የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም የቡድኑን ዝግጅት አስመልክቶ መግለጫ የሰጡ ሲኾን አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። አሠልጣኙ ከምድብ አለማለፋችንን ብናረጋግጥም ታሪካዊውን ጨዋታ ለማሸነፍ ተጫዋቾች በአካልም በሥነ-ልቦናም ዝግጁ መኾናቸውን ገልጸዋል።

በምድብ አራት ከግብፅ ፣ ማላዊና ጊኒ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ በ4 ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ተቀምጣለች።
ከ2023 የኮትዲቫር የአፍሪካ ዋንጫ ውጭ መኾኗም ተረጋግጧል።

አሠልጣኝ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም “ከአፍሪካ ዋንጫው ብንሰናበትም ግብፅን ለማሸነፍ በሙሉ አቅም እንጫወታለን” ነው ያሉት።
እንደ ብሔራዊ ቡድን ወቅታዊ አቋማችንን የምንፈትሽበት ጨዋታ ጭምር ነው ብለዋል አሠልጣኙ።
ከግብፅ ጋር የተደረገውን የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ 2 ለ 0 ማሸነፏ ይታወሳል።

ዘጋቢ፡- ባዘዘው መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጎንደር ከተማ አሥተዳር በፋሲል ክፍለ ከተማ የአገልግሎት አሰጣጥ ለእንግልት ዳርጎናል ሲሉ ተገልጋዮች ተናገሩ።
Next articleለመኸር እርሻ ከ4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ አርሶ አደሩ እጅ መግባቱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡