
አዲስ አበባ: ነሐሴ 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 14ኛ ዙር ስለ ኢትዮጵያ መድረክ እና የፎቶ አዉደ ርእይ በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ተምሳሌት በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነዉ።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሚዘጋጀዉ ስለ ኢትዮጵያ ባለፉት 13 ዙር ዉይይቱ ስኬታማ የመፍትሄ ሀሳቦች እንዲመጡ አድርጓል ብለዋል።
በዚህ ዙር አዲስ አበባ ከተማ ያከናወነቻቸዉ የልማት ተግባራት በፎቶ አዉደ ርእይ ይታያሉ ብለዋል ከንቲባዋ፡፡
መድረኩ ስለ አዲስ አበባ በሰፊዉ ይነሳልም ነው ያሉት።
አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና ፣የዲፕሎማሲ መቀመጫ መኾኗን ያነሱት ከንቲባ አዳነች ስለ አዲስ አበባ በጋራ መሥራት ያስፈልጋልም ነው ያሉት።
በመድረኩ የፓናል ዉይይት እየተካሄደ ሲኾን ስለ አዲስ አበባ እና ስለ ኢትዮጵያ እድገትም ሀሳቦች ተነስተዋል።
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉኡሽ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!