ጎንደር ከተማ ወደ ሰላም መምጣቷን ተከትሎ ተጥሎ የነበረው የሰዓት ገደብ ወደ ምሽት 2:00 ሰዓት ተሻሻለ።

64

ጎንደር: ነሐሴ 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የአስቸኳይ ጊዚ ዓዋጅ መታወጁ ይታወሳል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተጣለው የሰዓት ገደብ ከነሀሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ማሻሻያ መደረጉን የከተማ አሥተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ረዳት ኮሚሽነር አየልኝ ታክሎ ገልጸዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተጣለው የሰዓት ገደብ እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት የነበረው የተሽከርካሪና የሰዎች እንቅስቃሴ እሰከ 2:00 ሰዓት መሻሻሉን ረዳት ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

በከተማዋ አንጻራዊ ሰላም እንዲመጣና የሰዓት ገደቡ እንዲሻሻል የከተማዋ ወጣቶችና ነዋሪዎች ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ኮማንድ ፖስቱ በቀጣይም ቢሆን ያለውን ሰላም እየገመገመ የሚስተካከሉ ክልከላዎች እንደሚሻሻሉም ገልጸዋል።

መጭው ወቅት የዘመን መለወጫ ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አሁን ላይ ያለው ሰላም ቀጣይነት እንዲኖረው ማኅበረሰቡ እያደረገ ያለውን እገዛ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ረዳት ኮሚሽነር አየልኝ ታክሎ አመላክተዋል።

ዘጋቢ፦ ደስታ ካሳ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጋምቢ ህክምና እና ቢዝነስ ኮሌጅ ለ16ኛ ጊዜ በተለያዩ መርኃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ከ500 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ።
Next articleበሚቀጥሉት 10 ቀናት በሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ዝናብ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየቀነሰ ይሄዳል።