“በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሁሉም ዜጎች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እየተሰራ ነው” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

61

ባሕር ዳር: ነሐሴ 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሁሉም ዜጎች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአማሮ ኬሌ የማጻ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ የሚቻለው ትምህርትን ለሁሉም ማድረስ ሲቻል ነው ያሉት ሚኒስትሩ በገጠርም ሆነ በከተማ ሁሉም ዜጋ ጥሩ የትምህርት ዕድል እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በሁሉም ክልሎች ደረጃቸውን የጠበቁ 50 ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡም ጠቁመዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበባየሁ ታደሰ በበኩላቸው የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻልና የመቀየር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በአማሮ ኬሌ ከተማ ዛሬ የመሰረተ ድንጋይ የተቀመጠለት የማጻ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትሞህርት ቤት በዚህ ዓመት ከሚገነቡ 16 ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ መሆኑም ተገልጿል።

በሰዎች ለሰዎች ድርጅት የሚገነባው ይህ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 መጨረሻ ተጠናቅቆ በ2017 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ እንደሚጀምር ተጠቁሟል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አዲስ የተሸከርካሪ ሰሌዳ በአገልግሎት ላይ አዋለ፡፡
Next articleየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮርፓሬት ልዩ ደንበኞች የሚስተናገዱበትን ዓቢይ ቅርንጫፍ ሥራ አስጀመረ።