የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አዲስ የተሸከርካሪ ሰሌዳ በአገልግሎት ላይ አዋለ፡፡

182

ባሕር ዳር: ነሐሴ 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ለተዋጊ ክፍሉ ግዳጅ አፈፃፀም ተጨማሪ አቅም የሚሆኑ የተለያዬ ሞዴል ያላቸውን ቀላል ተሸከርካሪዎች ስታንዳርድ በማዘጋጀት ለዕዞችና ለክፍሎች የቁልፍ ርክክብ ተደርጓል፡፡

የተሸከርካሪዎችን ቁልፍ ለሁሉም ዕዞች እና ለተለያዩ ተዋጊ ክፍል አመራሮች ያስረከቡት የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል ተቋማችን መከላከያ የሠራዊቱን ዝግጁነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉና ተጨማሪ አቅም የሚሆኑ ተሸከርካሪዎችን ማደል መቻሉን ገልጸዋል።

ተቋሙ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረውን የተሸከርካሪ ሰሌዳ በአዲስ ሠሌዳ የቀየረ መሆኑን እና ከነሃሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተሸከርካሪዎች ላይ በመለጠፍ አገልግሎት መጀመሩን የገለጹት ኅላፊው በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሁሉም የተቋሙ ተሸከርካሪዎች አዲስ ሰሌዳ እንደሚደርስም ገልጸዋል።

በተለያየ ምክንያት የተቋሙ በርካታ ሠሌዳዎች ከተቋሙ ዕውቅና ውጭ በሌሎች እጅ መገኘቱ ለሕገ-ወጥ ተግባር እንዳይውሉ ለመከላከል ታሳቢ ተደርጎ ሠሌዳው የተቀየረ መኾኑን ነው ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን የገለጹት።

አሁናዊ የሠራዊቱን ተልዕኮ እና ግዳጅ መነሻ አድርጎ በሚሰጡት አገልግሎት መሰረት በኮድ ጭምር ተለይተው የተዘጋጁ ናቸው ብለዋል ሲል የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo: Hagayya 30/2015
Next article“በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሁሉም ዜጎች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እየተሰራ ነው” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ