በተያዘው የመኸር ወቅት ከ17 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት መታረሱን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ ።

68

ባሕር ዳር: ነሐሴ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በ2015/16 የመኸር እርሻ ከ17 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት መታረሱን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መለስ መኮንን በ2015/16 የመኸር እርሻ እንዲሁም የበልግና የመስኖ የግብርና ሥራን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ከሌሎች ዓመታት በተለየ ዘንድሮ ከ17 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ መሬት መታረሱንም አስታውሰዋል።

ከዚህ ውስጥም ከ7 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር በላይ እርሻ በኩታ ገጠም የለማ መሆኑን መግለጻቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም ዘብ በመቆም የሀገርን ሰላም አስጠብቀን ልንዘልቅ ይገባል” የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አሥተዳዳሪ አሸተ ደምለው
Next article“ስንወያይ፣ ስንመካከር እና ስንደማመጥ ችግሮቻችን ሁሉ ከኛ በታች ይሆናሉ” ዶ.ር መንገሻ ፈንታው