
ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የከተማ ግብርናን በማጠናከር በምግብ ራስን መቻል፤ ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት እና የከተማን ውበት መጠበቅ እንደሚቻል የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ግብርና መመሪያ አስተውቋል፡፡
ልጆች የተመጣጠነ ምግብ እንዲመገቡ በማድረግ አእምሮአዊ ና አካላዊ እድገት እንዲኖራችው ማኀበረሰቡም በምግብ እራሱን እንዲችልና ጠንካራ ኢኮኖሚ እንዲገነባ በሀገር ደረጃ ” የሌማት ትሩፋት “ በሚል እየተሠራበት ይገኛል፡፡
በደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር 2 መቶ አራት ሄክታር መሬት በጓሮ አትክልት የተሸፈነ ሲኾን በዶሮ ልማት ዘርፍ በስፋት እየተሠራ እንደሚገኝ ነው ከከተማ አሥተዳደሩ ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡
የከተማ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ ኀላፊ አቶ መርሻ አይሳነው በዘርፉ ከ 11 ሺህ በላይ የማኀበረሰብ ክፍል የሥራ እድል የተፈጠረላቸው ሲኾን 3ሺህ የሚኾኑት ሴቶች ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ የገቡ መኾናቸውን አንስተዋል፡፡
የከተማ ግብርና በስፋት ለመሥራት ብዙ መሬት ሳይኾን የተሻለ እሳቤ አስፈላጊ ነው የሚሉት ኀላፊው በሚሠራው ሥራ የኑሮ ውድነቱን ማረጋጋት፣ ኢኮኖሚናን ማሳደግ ፤የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት እና የከተማን ውበት መጠበቅ ይቻላል ብለዋል፡፡
በከተማ አሥተዳደሩ ግንዛቤን በማስፋት የከተማ ግብርናን በሁሉም ኀብረተሰብ ክፍል ተደራሽ የማድረግ ሥራ በትኩረት የሚሠራበት መኾኑም ተገልጿል፡፡
ዘጋቢ፡- ገንዘብ ታደሰ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!