የትምህርትን ቤቶችን ገጽታ በመቀየር የትምህርት ጥራትን ለማምጣት የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ መከናወናቸውን የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ገለጸ።

55

ባሕር ዳር: ነሐሴ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ፍታለሽ ምህረቴ ለአሚኮ እንደገለጹት በብሔረሰብ አሥተዳደሩ 11 የዳስ ትምህርት ቤቶች እና 302 ደግሞ የዳስ ክፍሎች አሉ፡፡

በብሔረሰብ አሥተዳደሩ 11 ወረዳዎች አሉ፡፡ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያው የዳስ ትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻል ከጦርነት ቀጣና ውጭ ያሉ 5 ወረዳዎችን ሳይጨምር ባካሄደው እንቅስቃሴ በመንግሥት፣ መንግሥታዊ ባልኾኑ ድርጅቶች እና በኀብረተሰቡ ድጋፍ የተለያዮ ግንባታዎች ተከናውነዋል፡፡

በዚህም መሰረት 88 መማሪያ ክፍሎች ፣24 ብሎክ መጸዳጃ ቤቶች ፣3 ብሎክ ላብራቶሪ ክፍሎች እና 3 ብሎክ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ክፍሎች መገንባታቸውን ወይዘሮ ፍታለሽ ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ፋሲካ ዘለዓለም

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በበጀት ዓመቱ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በተከናወኑ ሥራዎች ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ ተተክተዋል” ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
Next articleፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ።