አዴት ከተማ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሷን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

159

ባሕር ዳር: ነሐሴ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ)በሰሜን ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ በአዴት ከተማ አሥተዳደር ዙሪያ በነበረው የሕግ ማስከበር ሥራ የሰው ሕይዎት ማለፉን እና ንብረትም መውደሙን ነዋሪዎች ለአሚኮ ገልጸዋል፡፡ሁኔታው ወዲያውኑ መርገቡም ተነግሯል፡፡ አሁን ላይ አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተመልሷል ነው ያሉት ነዋሪዎቹ። የንግድ ቤቶች በሙሉ አገልግሎት እየሰጡ መኾናቸውን እና የተሟላ ሰላማዊ የሰዎች እንቅስቃሴ መኖሩም ተገልጿል።

“ግጭት በሰዎች ሕይዎት እና በንብረት ላይ ጉዳት ከማድረስ ውጭ ሌላ ጥቅም የለውም” ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ሁሉም ማኅበረሰብ እና መንግሥት ለሰላማዊ ውይይት በሩን ክፍት በማድረግ ችግሮችን በውይይት እንዲፈቱም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጎብኚዎች ወደ ስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ እንዲመጡ ሰላም ወሳኝ መኾኑን የፓርኩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
Next article24ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ።