
ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰሜን ሸዋ ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስና መድሃኒት ድጋፍ አድርጓል። የቅርንጫፉ ኀላፊ አቶ ዳምጠው እምሻው ሆስፒታሉ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጫና የሚበዛበትና ባለፈውም ጊዜ በርካታ አገልግሎት ሲስጥ ስለነበር የቁሳቁስ ና የመድሃኒት ድጋፍ አስፈልጎታል ብለዋል። ለዚህም ችግሩን የሚያቃልልበት ድጋፍ ነው የተደረገው ብለዋል።
ወትሮውንም ቢኾን የመድሃኒት እጥረት የጤና ተቋማትን ተግባር የሚፈትን ነበር ያሉት የሆስፒታሉ ስራ ስኪያጅ የጸጥታ ችግር በሚያጋጥምበት ወቅት ደግሞ ክፍተቱ እንደሚሰፋም ገልጸዋል። ቀይ መስቀል ያደረገው ድጋፍ እንደዚህ አይነት ችግሮችን ያቃልላል ተብሏል። ድጋፉ ወቅቱን የጠበቀና የሆስፒታሉን ችግር ያገናዘበ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ለዓለም ለይኩን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!