
ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በ2016 የትምህርት ዘመን ከ5 መቶ ሺህ በላይ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ እቅድ ተይዟል፡፡ ይሁንና በዞኑ በነበረዉ የሰላም እጦት ሳቢያ የተማሪዎች ምዝገባ መቀዛቀዙን ነዉ የመምሪያዉ ምክትል ኀላፊ ታደሰ ሸዋፈራ የተናገሩት፡፡
በዞኑ ከሚገኙ ከ1ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች መካከል ምዝገባ እየተካሄደባቸዉ የሚገኙት ከ450 የማይበልጡት ናቸዉ ተብሏል፡፡
በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያለዉ የምዝገባ ሂደት የተጓተተ ነዉ ያሉት ምክትል መምሪያ ኀላፊዉ እስካሁን መመዝገብ የተቻለዉ ከ8 ሺህ የማይበልጡትን ነው ብለዋል፡፡ በዞኑ ካሉ 23 የትምህርት መዋቅር ባለባቸዉ ወረዳዎች መካከል በ18ቱ ምዝገባ የተጀመረ ቢኾንም ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ መግባት አልተቻለም ነው የተባለው፡፡
በተቀዛቀዘው የተማሪዎች ምዝገባ ምክንያት የትምህርት ዘመኑ መርሃግብር እንዳፋይለስ እየተሰራ ስለመኾኑ አቶ ታደሰ አስረድተዋል፡፡ በክልሉ ትምህርት ቢሮ የምዝገባ መርሐ ግብር መሰረት ሁሉንም ተማሪዎች ለመመዝገብ ጥረት ይደረጋልም ተብሏል፡፡ ምዝገባ ማከናወን በሚቻልባቸዉ አካባቢዎች በቸልተንነት ስራቸዉን በማይወጡ የትምህርት ዘርፍ አመራርና ባለሙዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳልም ብለዋል ምክትል መምሪያ ኀላፊዉ፡፡
ከነሃሴ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሁሉም ባለሙያና የትምህርት አመራር በመደበኛ ስራዉ መገኘት አለበት ያሉት አቶ ታደሰ አንፃራዊ ሰላም ባለባቸዉ የዞኑ ቦታዎች ሁሉ የተማሪ ምዝገባ ላይ ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ኤልያስ ፈጠነ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!