
አዲስ አበባ: ነሐሴ 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአደጋ ቀውስ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃን ቀድሞ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል የ55 ሚሊዮን ዩሮ ለአራት ሀገራት ድጋፍ ተደርጓል።
ክፍለ አህጉራዊ የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ እና አደጋ ስጋት ቅነሳ የምክከር መድረክ በሳይንስ ሙዚየም እየተካሔደ ነው።
ይህ ጉባኤ በዚህ ዓመት በግብፅ ሻርማል ሸክ በተካሔደው የተመድ የአየር ንብረይ ለውጥ ጉባኤ የአየር ንብረት እና አየር ጸባይ ጉዳት ለመከላከል የተላለፈው ውሳኔን አስመልክቶ የሚካሔድ ነው።
የምክከር ስብሰባው ውኃን መሰረት አድርጎ የአደጋ ቀውስን መከላከል በሚል ኢትዮጵያን ቀድሞ በመምረጥ በሱዳን፣ በኡጋንዳ እና በደቡብ ሱዳን የሚካሔድ ነው።
የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዴዔታ ዶክተር አብርሃም አዱኛ በዚህ ጉባኤ ሀገራቱ ለአደጋ ቀውስ ቅደመ መከላከል እና መረጃ ተደራሽነት እንዲሁም የገንዘብን ምንጭ የማግኘት ዓላማ ያለው መኾኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ ኤምባሲ የውኃ ዋና ጸሐፊ ጀልመር ቫን ቬን በአየር ንብረት ለውጥ የሚደረግ መተጋገዝ የጋራ ጉዳይ መኾኑን ጠቅሰዋል። የአደጋ ቀውስ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃን ማሳደግ ችግሩን ከ30 እሰከ 40 በመቶ ይቀርፋልም ብለዋል። በኢትዮጵያ፣ በሱዳን ፣ በኡጋንዳ እና በደቡብ ሱዳን የሚተገበር የ55 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ መንግሥታቸው ማድረጉን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!