በደብረታቦር ከተማ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

34

ባሕር ዳር: ነሐሴ 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደሯ ደብረታቦር ከተማ ባለፉት ቀናት በነበረው የሕግ ማስከበር ሥራ በሰው ሕይዎት እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

አሁን ላይ በከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ያለ ሲኾን ከዛሬ ነሐሴ 24/2015 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ መደበኛ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ነዋሪዎች ለአሚኮ ተናግረዋል።

ከሞተር ሳይክል እና ከባጃጅ ውጭ የኾኑ ሌሎች ተሽከርካሪዎችም በወትሯዊ የአገልግሎት ስምሪታቸው ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል።

ባንክ ቤቶችን ጨምሮ ሱቆች እና ሌሎችም የንግድ ተቋማት ክፍት ኾነው አገልግሎት እየሰጡ ነው። የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም ለአገልግሎት ክፍት ናቸው።

“ግጭት እና አለመረጋጋት ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴን በእጅጉ ይጎዳል፤ አላስፈላጊ የሕይወት መስዋዕትነትም ያስከፍላል” ያሉት ነዋሪዎቹ ለዘላቂ ሰላም መስፈን በትብብር መሥራት ያስፈልጋል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

ሕዝቡ እና መንግሥት ግልጽ ውይይቶችን በማድረግ እና ለሚነሱ ችግሮች ዘላቂ እና አፋጣኝ እልባት መስጠት ያስፈልጋል ነው ያሉት ነዋሪዎች።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበ2015 በጀት ዓመት ወደውጭ ከተላኩ ምርቶች 139 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለጸ፡፡
Next articleኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብርን ያጠናክራል – ቻይናውያን ፕሮፌሰሮች