
ባሕር ዳር: ነሐሴ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በጋራ የሚሳተፉበት የአፍሪካ ሲንጋፖር ቢዝነስ ፎረም 2023 በሲንጋፖር እየተካሄደ ይገኛል።
በፎረሙ ኢትዮጵያን በመወከል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሚ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ኃላፊዎቹ በቆይታቸው ከተለያዩ አለም አቀፍ አምራቾችና ዲፕሎማቶች ጋር ውይይቶችን እያካሄዱ መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህም ለኢትዮጵያ አዲስ ኢንቨስትመንት በማምጣት በኩል ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
በመድረኩ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ እንደ አንድ ትልቅ የኢንቨስትመንት ዕድል መተዋወቁም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ ያመለክታል።
በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ አጠቃላይ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የተዘጋጁ መሰረተ ልማቶችና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችም መቅረባቸው ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!