በ19ኛው የቡዳፒስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ገባ።

51

ባሕር ዳር: ነሐሴ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሀንጋሪ ቡዳፔስት ሲካሄድ በቆየው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው ለልዑኩ ደማቅ አቀባበል አድርገውታል።

ቡድኑ በሀንጋሪ ቡዳፔስት በነበረው ተሳትፎ ለኢትዮጵያ 2 የወርቅ፣ 4 የብርና 3 ነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን አስገኝቷል።

በዚህም ውጤት ከዓለም ስድስተኛ ከአፍሪካ ደግሞ የሁለተኛነት ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ነው ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ የገባው።

በባዘዘው መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በአንድነትና በመተባበር ስንሰራ ውጤቱ ያማረ እንደሚሆን የአትሌቶቻችን ድል አድራጊነት ለሌላውም አስተማሪ ነው” የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Next articleጸጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያቋረጡ ተማሪዎችን ለመፈተን ዝግጁት መጨረሱን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡