“ከፍትሕ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የኾነ አሠራር እንዲኖር የክልል ፍትሕ ቢሮዎች እየተገናኙ የልምምድ ልውጥ ሊያደርጉ ይገባል” የፍትሕ ሚኒስቴር

63

አዲስ አበባ: ነሐሴ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 4ኛው የፍትሕ ሚኒስቴር የክልል ፍትሕ ቢሮዎች እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቋማት የጋራ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በየስድስት ወሩ የሚካሄደው ይህ የጋራ መድረክ ከነሐሴ 23 እስከ 24 2015 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ነው።

በመድረኩ የፍትሕ ሚንስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎችም እየተሳተፉ ነው የሚገኙት።

የ2015 ዓ/ም የፌድራልና ክልል ፍትሕ አፈጻጸም ግምገማ የመወያያ ነጥቦች

👉 የፍትሕ አሰጣጡን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት የክልል ፍትሕ ቢሮዎች ባዘጋጇቸው እቅዶችና ፍኖተ ካርታዎች ላይ መወያየት

👉 የማኀበረሰብ ተኮር ፍትሕ አገልግሎትን ለማሳድግ ተሞክሮዎችን ማበረታታት

👉 የፍትሕ ዘረፉ የሚጠበቀውን ለውጥ እንዲያመጣ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ሊተገበሩ በታሰቡ ቁልፍ ተግባራት ላይ ውይይት ማድረግ ናቸው።

ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleብሪክስ የጋራ ተደማጭነትን በማሳደግ አባል ሀገራቱ ያላቸውን ጥቅም የሚያስጠብቅ ጥምረት መኾኑን ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሌ በሻህ ተናገሩ።
Next articleበ19ኛው የቡዳፒስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ገባ።