የአማራ ባንክ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፤ ከ70 ሺህ በላይ ሰውም ባለአክሲዮን ሆኗል፡፡

437

የአማራ ባንክ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፤ ከ70 ሺህ በላይ ሰውም ባለአክሲዮን ሆኗል፡፡

በምሥረታ ላይ የሚገኘው የአማራ ባንክ የ4 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር አክሲዮን ማስፈረሙን አስታወቀ፡፡ ባንኩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው ከዚህ ውስጥ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተደርጓል፤ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎችም ባለአክሲዮን ሆነዋል፡፡

በአክሲዮኑ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ለማሳተፍ እና ጠንካራ የገንዘብ አቅም ለመፍጠር የአክሲዮን ሺያጭ ጊዜውን ለሁለት ወራት እንዳራዘመም አስታውቋል፡፡ ዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2012ዓ.ም ሊጠናቀቅ የነበረው የአክሲዮን ሽያጭ እስከ የካቲት 30 ቀን 2012ዓ.ም መራዘሙን ነው አደራጅ ኮሚቴው ያስታወቀው፡፡

ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ -ከአዲስ አበባ

Previous articleበኩር ታኅሳስ 27-2012 ዓ/ም
Next articleበሰው ሰራሹ ሞሉ ሐይቅ ላይ ወጣቶች በዓሣ ማስገር እንዲሰማሩ እየተሠራ መሆኑን የኤፍራታና ግድም ወረዳ አስተዳድር አስታወቀ፡፡