ኢትዮጵያ በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 6ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች።

53

ባሕር ዳር: ነሐሴ 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከዓለም 6ኛ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች።

በቡዳፔስት ናሽናል አትሌቲክስ ሴንተር ስታዲየም ከነሐሴ 13 ቀን 2015 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ሻምፒዮና ተጠናቅቋል።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 2 የወርቅ፣ 4 የብር እና 3 የነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

በዚህም ከዓለም ስድስተኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ነው ሻምፒዮናውን ያጠናቀቀችው።

አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ስፔንና ጃማይካ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ በቅደም ተከተል ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ኬንያ በ3 የወርቅ፣በ3 የብር እና በ4 ነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም 5ኛ ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች።

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2022 በአሜሪካ ኦሬጎን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ4 የወርቅ፣በ4 የብርና በ3 የነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎች በማግኘት አሜሪካን ተከትላ 2ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበቡዳፔስቱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለተሳተፈው ልዑካን ቡድን ነገ አቀባበል እንደሚደረግ ባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
Next article“በአማራ ክልል 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ወጣቶች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ እየተሳተፉ ነው” የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ