
ባሕር ዳር: ነሐሴ 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በ19ኛዉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቡዳፔስት ለተሳተፈው ልዑካን ቡድን ነገ አቀባበል እንደሚደረግ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳ ገለጸዋል፡፡
የቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያ ጥሩ ውጤት ያገኘችበት እንደነበርም ተናግረዋል ። 2 ወርቅ ፣ 4ብርና 3 ነሃስ ሜዳሊያዎች ማገኘቷንም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
የተገኘው ውጤት የኢትዮጵያን ገፅታ የገነባ በመኾኑ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ለአትሌቲክስ ልዑኩ ነገ ነሐሴ 23/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል እንደሚደረግም ነው የተናገሩት። እስከ 2 ሰዓት ከሚደረገውን አቀባበል ቀጥሎ አትሌቶቹ በአውራ ጎዳናዎች በመዘዋወር ከሕዝቡ ጋር ደስታቸውን እንደሚገልጹም ተመልክቷል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!