
ባሕር ዳር: ነሐሴ 21/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ተቋርጦ የነበረው የሶስትዮሽ የህዳሴ ግድብ ድርድር በዛሬው እለት በግብፅ ካይሮ መጀመሩን የመንግሥት የሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
የሶስትዮሽ ድርድሩ ከዚህ በፊት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አቡዳቢ ሲደረግ ቆይቶ ረቂቅ ስምምነት ማዘጋጀት ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ከዛ ወዲህ ድርድሩ ሳይካሄድ ቆይቷል።
ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በቅርቡ በግብፅ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ጋር በደረሱት ስምምነት መሰረት የሶስትዮሽ ድርድሩ ዳግም ተጀምሯል። በዚህም ረቂቅ ስምምነቱ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይትና ድርድር እንደሚደረግ ተጠቁሟል።
ድርድሩ የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት እና የወደፊት የመልማት መብት ባስከበረ መልኩ ለማካሄድም አስፈላጊው ዝግጅት ተከናውኗል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!