ኢትዮጵያ በወንዶች ማራቶን የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች፡፡

53

ባሕር ዳር: ነሐሴ 21/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 9ኛ ቀኑን በያዘው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያ በወንዶች የማራቶን ውድድር ተጨማሪ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

ሀንጋሪ ቡዳፔስት እያስተናገደችው ባለው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን የወንዶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያ በልዑል ገብረ ሥላሴ አማካኝነት የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች፡፡

የ18ኛው ዓለም አትሌቲክስ ውድድር አሸናፊ የነበረው ታምራት ቶላ በ19ኛው የቡዳፔስት ዓለም ሻምፒዮን በማራቶን ያለኮታ ተሳትፏል፡፡ ታምራት ቶላ በውድድሩ ቀጥታ ተሳታፊ መሆኑን ተከትሎ በርቀቱ አራት አትሌቶችን የማሰለፍ እድል ያገኘችው ኢትዮጵያ በታምራት ቶላ፣ ፀጋየ ጌታቸው፣ ልዑል ገብረ ሥላሴ እና ሚልኬሳ መንገሻ ተወክላለች፡፡

በውድድሩ ኡጋንዳዊው ቪክቶር ኪፕላጋት ወርቅ ሲያገኝ፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊ እና ለእስራኤል የሚሮጠው ማሩ ተፈሪ ሁለተኛ በመውጣት ብር ሲያገኝ ልዑል ገብረ ሥላሴ ሦስተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡

በታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሰው ሠራሽም ኾነ የተፈጥሮ አደጋዎች ቢከሰቱ መረጃ ማግኘትና ምላሽ መሥጠት እንዲቻል ለክልሉ ወደሰላም መመለስ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባላል” የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
Next articleጅግዳን ኮሌጅ በርቀት፣ በቀንና በማታ በተለያዮ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 319 ተማሪዎች አስመረቀ።