
ባሕር ዳር: ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር በዓለ ሲመት በባሕርዳር ከተማ ተካሂዷል። በበዓለ ሲመቱ ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ አዲስ ለተሾሙት መሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
በአስቸጋሪ ወቅት ክልሉን ለመሩት ለቀድሞው ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ምሥጋና አቅርበዋል።
በአማራ ክልል የተፈጠረው ችግር በአጭር ጊዜ መሻሻል በማሳያቱ የተሰማቸውን ደስታም ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ከገባበት ችግር ወጥቶ ለሀገር ምሳሌ እንደሚኾን እተማመናለሁ ነው ያሉት። የሶማሌ ክልል ከአማራ ክልል ጎን መኾኑንም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!