
ባሕር ዳር: ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ርእሰ መሥተዳድር በዓለ ሲመት በባሕርዳር ተካሂዷል። በበዓለ ሲመቱ የተገኙት የአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ የአማራ ችግር የአፋር ችግር ነው ፤ አማራ የሰውነታችን አንድ አካል ነው ፤ አማራ ተረበሸ ማለት ኢትዮጵያ ተረበሸች ማለት ነው፣ ኢትዮጵያ ስትረበሽ ለጠላት በር እንከፍታለን ብለዋል።
በቤተሰብ ችግር ሲከሰት ለጠላት እጅ መስጠት ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ በአንድነት ችግሮችን ማለፍ ይገባል ነው ያሉት።
የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች አሉት ፤ ጥያቄዎችን እንዴት እንፍታ የሚለው ነው ወሳኙ ጉዳይ ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።
ለመሪዎች የመሪነት እድል መስጠት እና መሪዎችን ማገዝ ችግርን ይፈታል ነው ያሉት። የአፋር ክልል መንግሥት እና ሕዝብ ከአማራ ሕዝብና መንግሥት ጎን ነውም ብለዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!