“የአማራ ክልል ድል ድላችን ነው ፤ ፈተናውም ፈተናችን ነው” አቶ ሽመልስ አብዲሳ

83

ባሕር ዳር: ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር በዓለ ሲመት በባሕርዳር ተካሂዷል። በበዓለ ሲመቱ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ፈተና ገጥሟት ያውቃል ሁሉንም እያሸነፈች እዚህ ደርሳለች ብለዋል። አሁን የገጠማትን ፈተናም ታሸንፋለች ነው ያሉት።

በአማራ ክልል የገጠመው ችግር በሌሎች አካባቢዎች እንደሚገጥመው የገጠመ መኾኑንም ገልጸዋል። የቀድሞው የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በዘመናቸው ለሕዝቦች አንድነትና ልማት ተጠቃሚነት ታላቅ ነገር መሥራታቸውንም ተናግረዋል። የክልላቸው ሕዝብ በተፈለገበት ጊዜ ሁሉ ለአማራ ሕዝብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው የገለጹት። የአማራ ክልል ድል ድላችን ነው ፈተናውም ፈተናችን ነው ፤ ሁሉንም በጋራ እናሳካለን ብለዋል።

የተሻለችውን ኢትዮጵያ በልጆቿ መሥዋእትነት ለልጆቻችን እናስረክባለን ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ በመልእክታቸው።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ
Next article“የአማራ ችግር የአፋር ችግር ነው፤ አማራ የሰውነታችን አንድ አካል ነው” አቶ አወል አርባ