የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በዓለ ሲመት እየተካሄደ ነው።

267

ባሕር ዳር: ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አዲሱ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በዓለ ሲመት እና የሥራ ርክክብ ሥነ ሥርዓት በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል ተመስገን ጥሩነህ፣ የቀድሞው የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች፣ ጄኔራሎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ነሐሴ 19/2015 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የቀድሞውን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ አቶ አረጋ ከበደን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አድርጎ ሾሟል። ዛሬ ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም የአዲሱ ርእሰ መሥተዳድር በዓለ ሲመትና የሥራ ርክክብ እየተካሄደ ነው። አዲሱ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አዲስ ካቢኔ በምክር ቤቱ አቅርበው ማፀደቃቸው ይታወሳል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች በአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር በዓለ ሲመት ለመታደም ባሕርዳር ገቡ።
Next article“ያለ አግባብ ትንኮሳዎችን እና የፖለቲካ ሥራዎችን በግልፅ በመታገል ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ እንድናጸና አደራ እላለሁ” አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ