
ባሕር ዳር: ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች በአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር በዓለ ሲመት ለመታደም ባሕርዳር ገብተዋል። ርእሳነ መሥተዳድሮቹን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተሰፋዬና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። የአማራ ክልል ምክር ቤት ትናንት ነሐሴ 19/2015 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ጉባዔ የቀድሞውን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ አቶ አረጋ ከበደን ርእሰ መሥተዳድር አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።
ትናንት የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙት አረጋ ከበደ በዓለ ሲመት ዛሬ በባሕር ዳር ይካሄዳል።
ርእሳነ መሥተዳድሮች ባሕር ዳር የገቡት በአዲሱ ርእሰ መሥተዳድር በዓለ ሲመትና የሥራ ርክክብ ለመታደም ነው።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!