የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ሁለት ልዩ ልዩ ሹመቶችን ሰጡ።

251

ባሕር ዳር: ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታውን በጥልቀት በመገምገም የአመራር ሪፎርም እየሠራ ይገኛል። ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ሁለት ልዩ ልዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።
በዚህም መሰረት፦

1. አቶ ፍስሃ ደሳለኝ የርእሰ መሥተዳድሩ የሕዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት አማካሪ
2. ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) የርእሰ መሥተዳድሩ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ ሆነው ተሹመዋል።

ሁሉም ተሿሚዎች በዞን እና በክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነቶች ላይ የሠሩ ሲሆን የላቀ ዕውቀትና ብቃት፣ ቁርጠኝነት እና ታታሪነት ያላቸው ስለመሆኑ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያሳያል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየቡዳፔስት ሌላ ክስተት!
Next articleየክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች በአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር በዓለ ሲመት ለመታደም ባሕርዳር ገቡ።