
ባሕር ዳር: ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) እጅግ አስቸጋሪ በሆነው የ42 ኪሎ ሜትር ርቀት የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያ ሌላኛውን የቡዳፔስት ክስተት አስመዝግባለች፡፡ ፈታኝ እና እልክ አስጨራሽ በሆነው የማራቶን ውድድር በሴቶች ኢትዮጵያ የወርቅ እና ብር ሜዳሊያ አሸንፋለች፡፡ አትሌት አማኔ በሪሶ የወርቅ እና ጎይቶም ገብረ ሥላሴ ደግሞ ሁለተኛ በመውጣት ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ ያለምዘርፍ የኋላው አምስተኛ በመውጣት አጠናቃለች፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!