አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሆነው ተሾሙ፡፡

598

ባሕር ዳር: ነሐሴ 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፤ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፤ 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ የክልሉን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ማዕከል አድርጎ ሲመክር ውሏል፡፡ ከውይይቱ በኋላ በክልሉ ወጥ የሆነ ሪፎርም ተግባራዊ ማድረግ እንደሆነ የጋራ መግባባት ላይ ደርሷል፡፡

የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ያቀረቡትን የመልቀቂያ ጥያቄ የተቀበለው ምክር ቤቱ በምትካቸው አቶ አረጋ ከበደን የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር በማድረግ ሹሟል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleርእሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ያቀረቡትን የስልጣን መልቀቅ ጥያቄ ምክር ቤቱ ተቀበለ።
Next articleየደብረ ብርሀን ከተማ መምሪያ ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ምቹ የማድረግ ሥራዎች መከናወናቸውን ገለጸ።