አቶ ወርቁ አይተነው ቃል የገቡትን የአምስት ሚሊዮን ብር ገቢ ማድረጋቸውን የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው አስታወቀ፡፡

441

ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 23/2012ዓ.ም (አብመድ) በሞጣ ከተማ አስተዳደር ከሰሞኑ የደረሰውን የሃይማኖት ተቋማት ቃጠሎ በማውገዝ ለመልሶ ግንባታ የሚውል የአምስት ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተው የነበሩት ባለሀበት አቶ ወርቁ አይተነው ገንዘቡን ገቢ ማድረጋቸውን የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ለአብመድ አስታውቋል፡፡

አቶ ወርቁ ለተቃጠሉ መስጂዶች መልሶ ግንባታ የሦስት ሚሊዮን እና ለጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን መልሶ ግንባታ የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ዘግበን ነበር፡፡
ትናንት ኮሚቴው ለአብመድ እንዳስታወቀው አቶ ወርቁ አይተነው ቃል የገቡትን ድጋፍ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥር ማስገባታቸውን አስታውቋል፡፡

ኮሚቴዎች ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ሁሉ በሚከተሉት የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉም አስታውቋል፡፡

• ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000313465091
• ዓባይ ባንክ 2231111333392020
• አዋሽ ባንክ 01320278548100
• አቢሲኒያ ባንክ 24512339
• ኅብረት ባንክ 2610416783616012
• ቡና ባንክ 2219501002457

Previous articleየቤት ሠራተኞች የሕግ ከለላ ባለማግኘታቸው የጉልበት ብዝበዛና የሞራል ጫና እየደረሰባቸው እንደሆነ ተናገሩ፡፡
Next articleከ7 ሺህ ቶን በላይ የማር ምርት መገኘቱን የአማራ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡