በ2016 ዓ.ም አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የመንግሥትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚተገበር የትሞህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

57

ባሕር ዳር: ነሐሴ 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪ መጻህፍትና የመምህራን መምሪያዎችን ለመምህራንና ባለድርሻዎች ለማስተዋወቅ የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ (ዶ.ር) ስርዓተ ትምህርቱ የሚተገበረው ከዓለም አቀፍና ከውጭ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች በስተቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሚያስተምሩ ሁሉም የመግስትና የግል ትምህርት ቤቶች መሆኑን ገልጸዋል።

ስርዓተ ትምህርቱም በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በትግራይ ክልል ደግሞ በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል እንደሚተገበርም ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕዝቡ ከመንግስት ጎን በመሆን የሰላም አማራጭን መፍትሄ አድርጎ እንዲወስድ የምክር ቤት አባላት አሳሰቡ።
Next articleየትምህርት ዘመኑን በሥኬት ለማጠናቀቅ የቅድመ ዝግጅት ሥራው መሠራቱን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።