
ባሕር ዳር: ነሐሴ 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የመምሪያዉ ተወካይ ኀላፊ እና የማኅበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ዋና ክፍል ኀላፊ ምክትል ኮማንደር ጥላሁን ደበበ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የፖሊስ ተቋማት እና ባልደረቦች ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል፡፡
በተቋማቱ ላይ ዘረፋና የንብረት ዉድመት ደርሷል ያሉት ምክትል ኮማንደሩ በተለያዩ ተቋማት ዉስጥ የነበሩ የተቋማትና የግለሰብ ሰነዶች እንዲወድሙ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡
በዞኑ ቀወት ወረዳና ሸዋሮቢት ከተማ ላይ በሚገኙ የፖሊስ ተቋማት ላይ የከፋ ጉዳት ስለመድረሱም አስረድተዋል፡፡
አሁን ላይ አንፃራዊ ሰላም በታየባቸዉ አካባቢዎች ተቋማቱን ወደ ሥራ ለማስገባት የድጋፍና ክትትል ሥራዎች እየተሠሩ ስለመኾናቸዉም አስታዉቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ኤልያስ ፈጠነ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!