ኢትዮጵያ እና ሕንድ ከብሪክስ ስብሰባ ጎን ለጎን በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ውይይት አደረጉ፡፡

37

ባሕር ዳር: ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 15ኛው የብሪክስ ስብሰባ ላለፉት ተከታታይ ሦስት ቀናት በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ተካሂዷል፡፡ ስብሰባው ሲጠናቀቅም ኢትዮጵያን እና ሌሎች አምስት ሀገራትን አባል ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ላለፉት ሦስት ቀናት በደቡብ አፍሪካ ጆሃንሰበርግ በተካሄደው 15ኛው የብሪክስ ስብሰባ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ እና ሕንድ አብረው ለመሥራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገልጸዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበር በተደረገው የብርክስ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ከመጪው ዓመት ጥር ጀምሮ አባል የምትሆንበትን ውሳኔ አሳልፏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗን ተከትሎ ከሕንድ ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችላትን ውይይት ከብሪክስ ስብሰባ ጎን ለጎን ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ብሪክስን እንድትቀላቀል ሕንድ ቁርጠኛ አቋም ነበራት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱ አብሮ ለመሥራት የሚያስችል ነበር ብለዋል፡፡ በግብርና፣ ቴክኖሎጂ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብሮችን የሚያጠናክሩ ውይይቶች መካሄዱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

በታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አለመግባባቶችን በሰከነ መንገድ መፍታት ይገባል” የደሴ ከተማ መንግሥት ሠራተኞች
Next article“ያልገቡን እየገቡን፣ ችግሮችን እየፈታን፣ አንድ እየኾን ለልጆቻችን የኩራት ምንጭ የኾነች ኢትዮጵያን መፍጠር ይኖርብናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)