“አለመግባባቶችን በሰከነ መንገድ መፍታት ይገባል” የደሴ ከተማ መንግሥት ሠራተኞች

59

ደሴ: ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ የመናፈሻ ክፍለ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች በወቅታዊ ጉዳይ ከምሥራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተቀስቅሶ በነበረው ጦርነት በርካታ ውድመት ደርሷል።

በወቅቱም በደሴ ከተማ በሰው ሕይወት እና በተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን ለአሚኮ አስተያየታቸውን የሰጡ የመናፈሻ ክፍለ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች አስረድተዋል፡፡ እየታዩ ያሉ ግጭቶችም ስጋት እንዳሳደረባቸው ነው የተናገሩት።

አለመግባባት እና ጥያቄዎች ካሉ በሰከነ መንገድ መፍታት ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።

በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች ተስፋፍተው ወደ ደሴ ከተማ እንዳይገቡ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ያሉት በደቡብ ወሎና ደሴ ከተማ ኮማንድ ፖስት የመናፈሻ ክፍለ ከተማ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ኮለኔል ዮናስ አዱኛ የከተማዋን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ከኅብረተሰቡ ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የሃይማኖት አባቶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ምሁራን በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች ሲፈጠሩ ወደ ሰላም ለመቀየር ኀላፊነታቸውን መወጣት እዳለባቸው የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ሌተናል ኮለኔል ዮናስ አዱኛ ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- ሰልሀዲን ሰይድ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በከተማዋ የእንቁላልና የወተት ምርት ከበቂ በላይ እየቀረበ ነው” የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽሕፈት ቤት
Next articleኢትዮጵያ እና ሕንድ ከብሪክስ ስብሰባ ጎን ለጎን በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ውይይት አደረጉ፡፡