ዓባይ ቴሌቪዥን የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ቸክና ደረሠኝ ተሰረቀ ብሎ ያቀረበው መረጃ ከእውነታ የራቀ መኾኑን ከተማ አሥተዳዳሩ አስታወቀ፡፡

26

ባሕር ዳር: ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረታቦር ከተማ አሥተዳዳር ገንዘብ መምሪያ ኀላፊ ማሩ አሠፋ ለአሚኮ እንደገለጹት የዓባይ ሚዲያ ቴሌቪዥን ነሐሴ 16/2015 ዓ.ም በቀኑ የ6 ሰዓት የቴሌቪዥን የዜና እወጃው ላይ የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳዳር ቸክ እና ደረሰኝ ጠፍቶበታል ተብሎ መታወጁ የተሳሳተና ከእውነት የራቀ መኾኑን አንስተዋል፡፡

ኀላፊው ከተማዋ ካለመረጋጋት ወጥታ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ በገባችበት በአሁኑ ወቅት እንደዚህ ዓይነት ሽብር የሚፈጥር የተሳሳተ መረጃ ማሰራጨት ከሥነ ምግባር ውጭ መኾኑን ነው ያነሱት፡፡

አቶ ማሩ እንዳሉት ዓባይ ሚዲያ እንደነዚህ ዓይት የመረጃ ምንጭ የሌላቸው መረጃዎች ሰዎች ላይ ሽብር ከመፍጠር ውጭ የሚያመጡት ጥሩ ነገር እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡

ከተማ አሥተዳዳሩ የቀን ከቀን ተግባሩን በሰላማዊ ኹኔታ እያካሄደ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ሚዲያው በቴሌቪዥን ጣቢያው እንደነዚህ ያሉ አላስፈላጊ ጉዳዮችን ለሕዝብ ማድረሱ በሕዝብ ሥነ ልቦና ላይ ያልተገባ ጫና የሚያሳድር በመኾኑ ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

ሀሰተኛ ዜናዎችን በማሰራጨት ላይ የተሠማሩ አካላለትን በማጋለጥ በኩል ሕዝቡ የራሱን ድርሻ እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡ የቀረበው መረጃ ከእውነት የራቀ በመኾኑ ኹሉም አካል የበኩሉን እንዲወጣ ሲሉም አሳስበዋል አቶ ማሩ፡፡

ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ትምህርት ቤቶችን ለመገንባትና የመማር ማስተማር ሥራውን በተሟላ መንገድ ለመምራት ሰላም አስፈላጊ ነው” የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
Next article“ውቧን የጎብኝዎች መዳረሻ ከተማ ባሕርዳርን የበለጠ ሰላሟ የተጠበቀ ለማድረግ እየሠራን ነው።” የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ባሕል ቱሪዝም መምሪያ