
ባሕር ዳር: ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን ተቀላቅላለች፡፡
እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር 2009 ላይ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ እና ቻይና የመሰረቱት ብሪክስ በዓመቱ ደቡብ አፍሪካን አባል ሀገር በማድረግ ቀላቀላት፡፡
ዛሬ ላይ ከ40 በላይ ሀገራት ሕብረቱን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላቸው ሲገለጽ 22 ሀገራት ደግሞ አባልነቱን ለመቀላቀል ግልጽ ደብዳቤ አስገብተዋል ተብሏል፡፡
በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ እየተካሄደ ባለው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በአዲስ ከተቀላቀሉ ስድስት ሀገራት አንዷ መሆኗ ተሰምቷል፡፡
“ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ታላቅ ስኬት ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የብሪክስ መሪዎች ኢትዮጵያን አባል ሀገር ማድረጋቸውን አድንቀዋል፡፡ በቀጣይም ኢትዮጵያ ብሪክስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያደርገውን ሁሉን አቀፍ ተደራሽነት እና ብልጽግና ትደግፋለች ብለዋል፡፡
አርጀንቲና፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ሳውዲ አረቢያ ከኢትዮጵያ ጋር ሕብረቱን የተቀላቀሉ ሀገራት ናቸው፡፡
በታዘብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!