የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በምክክር ሂደቱ ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራ ነገ ሊጀምር ነው።

138

አዲስ አበባ: ነሐሴ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የልየታ ሥራውም ከነሀሴ 18 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተግባር ይገባል ተብሏል። ለዚህ የተሳታፊዎች ልየታ አጋዥ የሚኾኑ ተቋማት ለይቻለሁ ያለው ኮሚሽኑ ለተለዩት ተቋማትም ስልጠና ሰጥቼ ወደ ተግባር አስገባለሁ ብሏል። ኮሚሽኑ በከተማ አሥተዳደሩ በሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ተግባር ውጤታማ ይኾን ዘንድ ከ119 ኙ የወረዳ አስተዳደሮች ጋር በመተባበር ተወካይ ተመርጦ ይሠራል ተብሏል።

በከተማ አሥተዳደሩ የሚደረገው የምክክር ተሳታፊዎችም የማኀበረሰብ ክፍሎችን፣ ፆታንና ሃይማኖታዊ ኹኔታን ታሳቢ ያደረገ ይኾናል ተብሏል። ለዚህ ማኀበረሰቡ ኀላፊነት በተሰማው መልኩ አጋዥ እንዲኾን ተጠይቋል።

ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የ2016 የትምሕርት ዘመንን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አጠናቅቂያለሁ” ትምህርት መምሪያው
Next articleየግጭት ወቅት ቅድሚያ ተጎጅዎች ሴቶች በመኾናቸው ለሰላም መስፈን ሊመክሩ እንደሚገባ ተገለጸ።